የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ መልዕክት

Message from the Head of Addis Ababa Prosperity Party

አቶ መለሰ ዓለሙ የአዲስ አበባ ብልጽግና ፓርቲ ኃላፊ H.E. Melese Alemu Head of Addis Ababa Prosperity Party

ትውልድ አላማ ሊኖረው ይገባል፡፡ የመለወጥ አላማ ፤ወደ ተሻለ ህይወት የመውጣት አላማ፤ ካለበት አስቸጋሪ ሁኔታ የመሻገር አላማ፡፡ የሰው ልጅ ከአላማ ውጪ ወዴት እንደሟዝ የማያውቅ ኮምፓስ የሌለው መርከብ እንደማለት ነው፡፡

ሰው በምድር ላይ የሚቆይበት ዘመን የተወሰነና አጭር ነው፡፡ ጥያቄው በዚህ ወቅት ምን አከናወንኩ?  የሰው ልጅን የሚጠቅም ምን ቁም ነገር አበረከትኩ ? የእኔ ቆይታ ምን ፋይዳ አለው ? የሚለው ነው፡፡ ይህንን ጥያቄ ህሊናውን በሚያረካ መልኩ መመለስ የቻለ ሰው እሱ የኖረበትን አላማ ያወቀና የተረዳ ነው! የራስ ፍላጎትን ብቻ እያረኩ መኖር ሰውን ከእንስሳ እኩል የሚያደርግ ሲሆን ስግብግብ ሰው ፍላጎቱ አይቆምም፡፡ መስራት መኖር ሌሎችን ማገዝ ለብዙሃን በሚጠቅም ቁምነገር ላይ መሰማራት፤ ከፍ ያለ ሰብአቁምነገር ነው፡፡

አቅማችን ውስን ቢሆንም፤ እውቀታችን የተገደበ ቢሆንም፤ ገንዘባችን ጥቂት ቢሆንም፤ ከየትኛውም ቤተሰብ ጎሳና ሃረግ ብንመጣም አንድ ታላቅ ነገር መስራት እንችላለን፡፡ አንድ ታላቅ ነገር ለመስራት ጊዜው አሁን ነው! ኢትዬጵያን ለመቀየር ደግሞ ነገ የሚባል ቀጠሮ የለውም፡፡

ውድ የብልፅግና አባላት እና ደጋፊዎቻችን የዚህ ታሪካዊ ፓርቲ አባላት ስለሆናችሁ ደስ ሊላችሁ ይገባል፡፡ ብልፅግና ትውልድ የሚቀይር ሃሳብ ይዞ  የተነሳ በኢትዮጵያ ታሪክ እጅግ ተራማጅና ሰውኛ ባህርይ ያለው የትውልዱ ፓርቲ ነው፡፡ በዚህ ታሪካዊ ፓርቲ ውስጥ አባል የሆናችሁ አባላትና ደጋፊዎች ከመላው ህዝብ ጋር ሆነን ኢትዮጵያን ወደ ብልፅግና እናምራ! 

ዓላማ

ተልዕኮ

እሴቶች

የብልጽግና ፓርቲ ዓላማ ጠንካራ ፤ ዴሞክራሲያዊና ቅቡልነት ያለው ዘላቂ ሀገረ መንግስት እና ልማታዊና ፍትሃዊ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጥ አካታች የኢኮኖሚ ስርዓት መገንባት እንዲሁም ሁለንተናዊ ብልጽግናን የሚያሰፍን ማህበራዊ ልማት ማረጋገጥ እና ሀገራዊ ክብርን ማዕከል ያደረገ የውጭ ግንኙነት ማካሄድ ነው ።
በከተማችን አዲስ አበባ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍሎች በፍትሀዊነት እና በእኩልነት ተጠቃሚ የሚያደርግ ጉዞ በብቃት በማስተባበርና በመምራት በሂደቱም የተሳለጠ ዲሞክራሲ ሁሉም ህዝቦች ያለአድልዎ የሚያሳትፍ የኢትዮጵያውያን የጋራ ራዕይና ጉዞ ተምሳሌት የሆነች ከተማ መፍጠር ነው!
የህዝቦች ክብር
ፍትህ
ህብረ-ብሄራዊ አንድነት

ዋና ዋና ዜናዎች

እርስ በእርስ ስንሻኮት የምናባክነው የህዝብ ሃብትና ጊዜ የለም!
አዲስ አበባ አዲስ የለውጥ መንገድ ላይ ናት፡፤
አዲሱ የከተማዋ አመራር ስራ ከጀመረ እነሆ ስድስት ወራት ተቆጠሩ፡፡ በነዚህ ስድስት ወራት በከተማዋ መሰረታዊ የሚባሉ የህዝብን ጥቅም የሚያስከብሩ ስራዎች ላይ ትኩረት ተደርጎ እንቅስቃሴ ተደርጓል፡፡
አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነቱን ጠብቆ ለከተማዋ ብልፅግና በጋራ ተንቀሳቅሷል፡፡
ከዚህ በፊት ይታይ እንደነበረው ጎራ ለይቶ በመፋለም ፤መዋቅሩን እስከታች ድረስ በራሱ ኔትወርክ በማደራጀት የህዝብን ጥቅም ከማስቀደም ይልቅ የራሱንና የጥቅም ስብስቡን ለማስደሰት መሯሯጥና እርስ በእርስ ሽኩቻ እና የቃላት መወራወር አሁን ሙሉ ለሙሉ ቀርቶ የከተማዋን ነዋሪ ታሳቢ ያደረጉ እንቅስቃሴዎች ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ ወደ ስራ ተገብቷል፡፡
በከተማዋ ተንሰራፍቶ የቆየውን ህገወጥነት ለመከላከል በቆራጥ አመራር በአንድ ልብ ተዘምቷል፡፡ በዚህም አስደናቂ ውጤቶች ተመዝግበዋል፡፡
ነገር ግን አሁንም ቀሪ ስራዎች አሉ፡፡ ስራው ተጀመረ እንጂ አልተጠናቀቀም፤ ትግሉ ተነካ እንጂ ጨርሶ ከስሩ አልተመነገለም፡፡ ጉዞው ወደፊት ነው፡፡….. የነብር ጭራ አይያዙ ከያዙም አይለቁ እንደሚባለው የተጀመረው ትግል ከግብ ሳይደርስ የሚመለስ የለም፡፡ ይህ መልካም ጅምር ይበልጥ እንዲጎመራ የከተማው ነዋሪ ከአስተዳደሩ ጎን በመሆን የጀመረውን ፍልሚያ እንዲያግዝ ጥሪ ቀርቦለታል፡፡ ህዝቡ ለዚህ በጎ እንቅስቃሴ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንዲያደርግ ይጠበቃል፡፡

ለዜጎቻችንን ተጠቃሚነትና ለከተማችን ብልፅግና እንደ አንድ ልብ ሆነን እንሰራለን!
በርካታ የህዝብ ጥያቄዎች አሉ፤የተከማመሩ የዘመናት ጥያቄዎችን የመመለስ ሃላፊነትም ተረክበናል፡፡ ይህንንም ለማሳካት ሌት ተቀን መስራት እንዳለብን አምነን በትጋት እየተንቀሳቀስን እንገኛለን፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት በተንቀሳቀስንባቸው መስኮች በእርግጥም የሚታይ ለውጥ ማምጣት ችለናል፡፡
ተደላድሎ የነበረውን የህገወጥነት መሰረት ከመሰረቱ ማናገት ችለናል፡፡ ያልተነኩ አጀንዳዎችን ነክተናል፡፡ ትግሉ ከኛ አልፎ ህዝባዊ እንዲሆን ህዝቡንም ማሳተፍ ጀምረናል፤ውስጣችንንም ለማጥራት ቁርጠኝነታችንን አሳይተናል፡፡
የነዋሪዎቻችንን የቆዩ ጥያቄዎ መመለስ ጀምረናል፡፡
አሁንም … የቅድሚያ አጀንዳችን የዜጎቻችንን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው፡፡ ግባችን የከተማችንን ብልፅግና እውን ማድረግ ነው፡፡ ለዚህ ደግሞ የአመራራችን አንድነት ወሳኝ መሆኑን እንረዳለን፡፡
ለሚከፋፍሉን አጀንዳዎች ጆሮ ሳንሰጥ ፤ ከውጪ በሚሰጠን አጀንዳ ሳንጠመድ ፤እንደ አንድ ልብ እያሰብን በአንድነትና በህብረት ተንቀሳቅሰን ከመዳረሻችን ከፍታ እንደርሳለን!
ብልፅግናችን ከህብረት ውጪ ሊሳካ አይችልም!!

“ብልፅግና የብርሃን ዘመን አብሳሪ!” – አቶ መለሰ ዓለሙ
ብርሃን የጨለማ ተቃራኒ ነው፡፡ ተቃራኒ ብቻ ሳይሆን የጨለማም አለቃ ነው፡፡ ጨለማ ብርሃንን ይቅደም እንጂ በብርሃን ይሸነፋል። ጨለማ ስበረታ የንጋትን መቃረብ ይነግራል።
አይን ቢወጉ እስከማይታይ ድረስ ቢበረታ እንኳ ለብርሃን ለቆ ይጠፋል። ከጨለማ ጀርባ ካለው ሃይል በላይ የብርሃን ሃይል ይልቃል። ለብርሃን መስራት ሃይል ያመነጫል። ብርሃን ለሁሉም ተስፋና መሻገር ይሆናል። ስራውም ያን ያህል ከባድ ነው። ለጨለማ መስራት ግን ማጥፋት ብቻ ይጠይቃል። የጥፋት አጋዥ አይጠፋምና። ነፋሱም ሲታቀብ ሃይል ለመስጠት ከባድ ፤ ለማጥፋት ግን በቀላሉ ይተባበራል። የማጥፋት ስራም እጅግ የቀለለ ነው። ብርሃን የሚያውጀው የጨለማን መረታት ፤ የጨለማን ክፋትና ጨቋኝነት ፤ የጨለማውን ውድቀት ነው፡፡
ፊታችን ያለው ዘመን የብርሃን ዘመን ነው። የኢትዮጵያውያን የመነሳት ዘመን ነው ፤ እይታችን ብርሃን ፤ ገቢራችን እውነትና እውቀት፣ መዳረሻችን ሁለንተናዊ ብልፅግና ነው!
አቶ መለሰ ዓለሙ
የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ

አምፖል የብርሃን ተምሳሌት ነው።

አምፖል ፍትሃዊነትንና ዕኩልነትን የወደፊት ርዕይንም ይገልጻል። የአምፖል ፊቱ በምስራቅ ወይም በምዕራብ ነው አይባልም። በሰሜን ወይም በደቡብ ነውም አይባልም። ከላይ ከከፍታው ወይም ከታች ከዝቅታው ነውም አይባልም። አምፖል ለሁሉም ፣ በሁሉም፣ የሁሉም ነው።

ብልጽግናም እንዲሁ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ፓርቲ ነው !!!

ክቡር አቶ አብርሐም አለኸኝ